የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚደረገውን ዘመቻ ለማገዝ የተነሳው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ሃይል ሽኝት ተደረገለት

0
722

የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚደረገውን ዘመቻ ለማገዝ የተነሳው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ሃይል በዛሬው እለት ሽኝት እንደተደረገለት ተገለፀ።

የጁንታው ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የከፈተውን ሀገር የመበታተን ተግባር ሙሉ በሙሉ በማክሸፍ የህዝቦችን አንድነት መመለስ የልዩ ሃይሉ ዓላማ መሆኑን የክልሉን ፕሬዝዳንት በመወከል አቶ ቢኒያም መንገሻ ተናግረዋል።

በፖለቲካው መድረክ ሽንፈትን የተከናነበው ይህ ስግብግብ ጁንታ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የቀበራቸው የተንኮል ፈንጅዎች ችግር የፈጠሩ ቢሆንም በሰላም ወዳዱ ህዝብና በሰራዊቱ ከፍተኛ ጥረት ሃሳቡ እንዳይሳካ ተደርጓል ብለዋል።

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ በበኩላቸው ይህ አጥፊ ቡድን ከውጭ የሀገራችን ጠላቶች ጋር በመቀናጀት የፈጸመው እኩይ ተግባር ምንጊዜም የታሪክ ተወቃሽነትን የሚያሳይ ነው በማለት ቡድኑን ለመደምሰስ አደራ የተሰጣቸው የልዩ ሃይል አባላት በድል አድራጊነት እንደሚመለሱ ሙሉ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስትን በመወከል ንግግር ያደረጉት ኮሎኔል ፋሲል ይግዛው በበኩላቸው የልዩ ሃይሉ አባላት በህወሓት ጠንሳሽነት በዞኑ የተፈጠረውን የሰላም ዕጦት ወደነበረበት ሳላም ለመመለስ የከፈሉት መስዋዕትነት የጀግንነታቸው ማሳያ ነው ብለው አሁንም በሰሜን ግንባር ተገኝተው ከሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመሆን ይህን አኩሪ ተግባር መፈጸም እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን ከመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here