በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በወላይታ ዞን ተካሄደ

0
548

በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ የታላቁ የህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውሀ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ በማስመልከት፣ በመንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀውን የህወሃት ቡድን ጥቃት በማውገዝ እና ለሀገር አንድነት ውድ ሕይወቱን እየከፈለ ላለው ለኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ክብር የመስጠት ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር እንድሪያስ ጌታ ለሰልፈኞች ባስተላለፉት መልዕክት የሀገራችን የሉዓላዊነት መገለጫና የባንዲራችን ፕሮጀከት የሆነው የታላቁ የህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውሀ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

የወላይታ ሕዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ወንድም ህዝቦች ጋር በመሆን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከታወጀበት ማግስት ጀምሮ ከዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙት እስከ ከፍተኛ ባለሀብት፣ ከመንግስት ሰራተኛ እስከ ጡረተኛ፣ከነጋዴ እስከ አርሶአደር ከአስተማሪ እስከተማሪ ቦንድ በመግዛትና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ግድቡ ለዚህ ደረጃ እንዲደርስ የበኩሉን ድርሻ መጫወቱን ጠቁመዋል።

የዛሬው የሕዳሴ ግድብ ስኬት እኛ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ከተነሳን ከባድ የሚባሉ ተግዳሮቶችን ማሸነፍ እንደምንችል ትልቅ ትምህርት ያገኘንበት በመሆኑ ሁሉም የዞናችን ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችን ጋር በመሆን በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን የገጠማትን ተግዳሮት ለመሻገር በጋራ እንዲነሳ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ሀገራችን ከ16ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ጀምሮ እስከ 20ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ማገባዳጃ ድረስ የተለያዩ የእሩቅና የቅርብ ጠላቶች ደግሞ የተቃጣባትን ወረራ የሀገራችን ህዝቦች በአብሮነት መንፈስ የሀይማኖት፣የቋንቋና የመልክአ-ምድራዊ አሰፋፈር ልዩነት ሳይገድበው፣ሳይለያይና ሳይከፋፈል ወራሪውን ሀይል በመመከት ሉአላዊነታችን በማስከበራቸው ለመላው የዓለማችን ህዝቦች በአርአያነት ሊጠቀስ በቅቷል ብለዋል፡፡

ይህንን አኩሪ ታሪክ ለመቀልበስ ብሎም የተዳከመች ኢትዮጵያን ያለመው የህውሃት ቡድን በህዝብ ፍላጎትና ትግል ዕውን ከሆነው የለውጥ ጎዳና በማፈንገጥ የህዝብና የሀገር አለኝታ በሆነው የመከላከያ ሰራዊት በፈጸመው ነውረኛ ጥቃት መነሻነት የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊታችን በወሰደው የህግ ማስከበር አርምጃ አከርካሪው ተሰብሯል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊታችን በወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ ወደ ሽፍታነት የተቀየረው የህወሀት ቡድን መንግስት ለህዝብ በመቆርቆር የሰጠውን የጥሞና ጊዜ እንደ ምቹ አጋጣሚ በመቁጠር ሽብርተኝነቱን ቀጥሏል፡፡

የህወሀት ቡድን ስግብግብ ፍላጎቱን ለማሟላት በለጋ ዕድሜ የሚገኙ ህጻናትን ጭምር ወደ ጦር ሜዳ በመሰማራት የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ በመሆኑ ድርጊቱን የዓለም ማህብረሰብ በጽኑ ሊያወግዘው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የህወሀት ቡድን እንዲደመሰስ መከላከያ ሰራዊታችን እያደረገ ላለው ተጋድሎ ስኬታማነት እንደ ሌሎቹ የሀገራችን ህዝቦች ሁሉ የወላይታ ዞን አስተዳደርና ህዝብ እንደ ቀደምት ጊዜያት ሁሉ ለሰራዊታችን የሚያደርገውን የማቴሪያል፣ የገንዘብ፣ የሞራልና ሌሎች ድጋፎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዶክተር እንድሪያስ አረጋግጠዋል።

በማያያዝም 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስ የገለጸው ሰላም ወዳዱ ህዝብ እንደ ወትሮው ሁሉ ሰላም ማስከበር የተጀመሩ የልማት ስራዎች ፍጥነትና ቀጣይነት እንዲረጋገጥ የድርሻቸውን በተነሳሽነት እንዲወጣ ማሳሰባቸውን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።።

የዕለቱ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ሳይበግራቸው የተገኙ ሰልፈኞች ለሀገር አንድነት የሚያስፈልገውን ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል።

 

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here