የሃገር መከላከያ ሠራዊትን መደገፍና ማገዝ በሚቻልበት ሂደት ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ዉይይት እያካሄዱ ነው።
የውይይት መድረኩን የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙና የሃገር መከላከያ ሠራዊት ተወካዮች እየመሩት ይገኛሉ።
“ክብር ለጀግናዉ የሃገር መከላከያ ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው በዚህ የውይይት መድረክ የከተማው ነዋሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላትና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች መሳተፋቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።





