የአብዬ 25ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ሰላም በማስከበር የሚያኮራ ውጤት ማስመዝገቡን ተገለፀ

0
448

አብዬ የሚገኘው የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ባለፉት ስድስት ወራት ሰላም በማስከበር በፈፀመው ግዳጅ ሀገርን የሚያኮራ ውጤት ማስመዝገቡን አስታወቀ፡፡

የሻለቃው ዋና አዛዥ ኮሎኔል ሌንጮ ኤደኦ እንደገለፁት፥ ሻለቃው ሲቪሎችን ከጥቃት በመከላከል፣ የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅና ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ በማድረግ በኩል ውጤታማ ተግባር መከናወኑን አስታውቀዋል፡፡

ሰላም አስከባሪው ማንኛውንም አይነት ፀረ-ሰላም እንቅስቃሴና ድርጊት በሰላማዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ብቻ ለመፍታት ከአካባቢው የጎሳ መሪዎች ጋር በጋራ በርካታ ስራዎችን እንደሰራ መግለጻቸውንም ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአካባቢው በህገ ወጥ መንገድ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን ተከታትሎ ትጥቅ በማስፈታትና ለፖሊስ በማስረከብ እንዲሁም ራሱንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ብሎም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞችን ከጥቃት በመከላከል ረገድ ውጤታማ ስራ መሰራቱንም የሻለቃው ዋና አዛዥ ተናግረዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here