የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በመደገፍና የህወሃትን ቡድን በመቃወምና በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ይገኛል

0
1268

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀውን የሕወሓት ቡድንን በወገንና በሀገር ላይ እያደረሰ ያለውን ጥፋት መቃወምና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍና አክብሮት ለመግለጽ በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ያነገቡ ወጣቶች፣ እናቶች፣ አርበኞች፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በስልፉ ላይ እየተሳተፉ ሲሆን የሀገርን ክብርና አንድነት የሚገልጹ ሙዚቃዎችንና መፈክሮችም በማሰማት ላይ ናቸው።

በድጋፍ ሰልፈኞቹ ከተያዙና በድምፅ እተሰሙ ከሚገኙ መፈክሮች ውስጥ :-
– ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚከፈል ዋጋ ክቡር ነው

– ኢትዮጵያ ላይ የሚውራረድ ሂሳብ የለም
-የምንዋጋው ጦርነት የህልውናና አገርን የማዳን ነው

– ኢትዮጵያ በጀግኖቿ አፍራ አታውቅም

-ግድባችን የሉዓላዊነታችን ተምሳሌት ነው

-ግድባችን ተሞልቶል፤ ኢትዮጵያችንም ከፍ ትላለች!

-ኢትዮጵያን መነጣጠል አይቻልም

-መከላከያ ሰራዊታችን የሉዓላዊነታችን ምልክት ነው

-ክረምቶች ቤት ፈርሰው የሚታደሱበት እንጂ ኢትዮጵያ የምትፈርስበት አይደለም

– ክብር ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን የሚሉት ይገኙበታል።

በተጨማሪም በሰላማዊ የድጋፍ ሰልፉ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁ እና የሕዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት መከናወኑን የሚያወድሱ ብዙ መፈክሮች እየተሰሙበት ይገኛል።

ሰላማዊ የድጋፍ ሰልፉ እስከ አጋማሽ ቀን የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here