ሁለተኛ ዙር የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት ለቀጠናው እድገትና ትብብር መለያ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

0
932

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በአካባቢው ችግር ካለመፍጠሩ ባሻገር ለቀጠናው እድገትና ትብብር መለያ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው በአረብኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መከናወኑን ገልፀዋል፡፡

ይህም በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ላይ ችግር እንደማይፈጥር ገልፀው ስጋት እንዳይኖርም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የህዳሴው ግድብ እውነተኛ ሀብት ሆኖ የጋራ ዕድገትና ትብብር መለያ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here