በኢትዮጵያ መንግስስ በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድን የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ ማፈትለኩን የወቅታዊ ሁኔታ የመረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡
በዕቅዱ መሠረት ከትግራይ ክልልና ከሱዳን አስርጎ በሚያስገባቸው ሠርጎ ገቦች አማካኝነት ጭፍጨፋውን እንደሚፈጽም ገልጿል።
ቡድኑ ይሄንን ለማድረግ እንዲመችው በራያና አፋር በኩል ተደጋጋሚ ትንኮሳ በመፈጸም የመከላከያ ሠራዊቱንና የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን ትኩረት በማዛባት የጦሩ ኃይል ወደ ራያና አፋር ሲሰባሰብና የምዕራቡ ኃይል ሲሳሳ በዚያ በኩል ጥቃት በመክፈት ድርጊቱን ለመፈጸም ማቀዱን እንደሚያሳይ ተገልጿል፡፡
የህውሓት ቡድን ከሰሞኑ የአማራ ልዩ ኃይልና መከላከያ በሑመራ ጭፍጨፋ እንደሚፈጽሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ማሠራጨት እንደሚጀምር ዕቅዱ ያሳያል ሲል የወቅታዊ ሁኔታ የመረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።
በተጨማሪም ቡድኑ ከሰሞኑ በአፋር ግንባር በፈጠረው ትንኮሳ ከአፋር ልዩ ኃይልና ከመከላከያ ሠራዊት ምላሽ እንደተሰጠው የተገለፀ ሲሆን በዚህ ትንኮሳ ወቅት ያሰለፋቸው ያልሠለጠኑ ሕጻናትና ሴቶችን መሆኑ ታውቋል።
ጁንታው ከአካባቢው ሲሸሽ ከ300 በላይ የሕጻናትና የሴቶች አስከሬኖችን በሲኖ ትራክ ጭኖ ወደ መቀሌ መሸሹም ታውቋል።
የደኅንነት ምንጮች እንደጠቆሙት ጁንታው በዚህ መልክ የሚያሸሻቸውን የሕጻናትና የሴቶች አስከሬኖች በአንድ መቃብር በመቅበር የጅምላ ግድያ የተፈጸመባቸው መቃብሮች አስመስሎ ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።



