በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሔደው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም ተጠናቅቋል፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ

0
660

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሔደው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጃው የህወሃትቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመቃወም፣ ለመከላከያ ሰራዊታችን እና ለሌሎች የሃገርን ህልውና ለማስጠበቅ ለተሰማሩ የፀጥታ አካላት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለፅ እና የሰራዊታችን ደጀን መሆናቸውን ለማሳየት እንዲሁም 2ኛው ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በሰላም መጠናቀቅን በማስመልከት ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ያደረጉት ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል፡፡

መርሃ ግብሩ በሰላም እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌደራል ፖሊስ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ተግባራቸውን ማከናወናቸውን በመጥቀስ በዚህ ስራ ላይ ለተሳተፉ እና ሃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ለመላው የከተማችን ነዋሪዎች በፍፁም ጨዋነት፣ በትዕግስት እና በተባባሪነት መንፈስ የፀጥታ አካሉን በመደገፋቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here