“ኢትዮጵያ ከፈተናዎቿ በላይ ሃያል ሃገር ናት!” – የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች

0
1289

የሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ እና የሌሞ ወረዳ ነዋሪዎችም የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እና የተለያዩ የህወሓትን ቡድን የሚያወግዙ መፈክሮችን በመያዝ ወደ አቢዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስቴዲየም እያመሩ ይገኛሉ

በደቡብ ኦሞ ዞን ጅንካ ከተማ በኢትዮጵያ መንግሰት በአሸባሪነት የተፈረጀውን የህውሃት ቡድን የሚያወግዝ እና ለመከላከያ ሰራዊታችን አጋርነትን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ህዝብ ኢትዮጵያ ከፈተናዎቿ በላይ ሃያል ሃገር ናት! በመሆኑም የኢትዮጽያን አንድነትና ሰላም የሚፈታተኑ ሀይሎችን በጋራ ለመመከት ተዘጋጅተናል ሲሉ ዛሬ በሰላማዊ ሰልፍ አረጋግጠዋል።

ሰልፈኞቹ የህውሃት ቡድን ስግብግብ ፍላጎቱን ለሟሟላት ሲል ህፃናትን ለጦርነት መማገዱን እንቃወማለን፤ ፈተናዎችን እየመከትን የተስፋ ብርሃናችንን ለማድመቅ እንሠራለን! የአሸባሪውን የህዋሃት ትንኮሳ እናከሽፋለን!፣ የአድሎ እጆች ከኢትዮጵያ ላይ ይነሳና በጁንታው ህውሃት የተቃጣብንን ትንኮሳ በማክሸፍ ሀገር ለማስቀጠል ተዘጋጅተናል በማለት መግለፃቸውን የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ አስታውቋል።

በተያያዘ ዜናም መሰል የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ በሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ እና የሌሞ ወረዳ ነዋሪዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ እና የሌሞ ወረዳ ነዋሪዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እና የተለያዩ አሸባሪው ድርጅትን የሚያወግዙ መፈክሮችን በመያዝ ወደ አቢዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስቴዲየም እያመሩ እንደሚገኙም የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ አስታውቋል።

የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ያነገቡ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ህጻናት፣ እናቶች፣ ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በስልፉ ላይ እየተሳተፉ ሲሆን፤ የሀገርን ክብርና አንድነት የሚገልጹ ሙዚቃዎችንና መፈክሮችን እያሰሙ እንደሚገኙም ተገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here