የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የ5ኛ 5 ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀመረ፡፡
ምክር ቤቱ በክልሉም ሆነ በሃገራችን በተፈጠሩ የተለያዩ የጸጥታ ችግሮች ለደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋትና መፈናቀል የሕሊና ጸሎት በማድረግ ነው ጉባዔውን ማካሄድ የጀመረው፡፡
ምክርቤቱ ለሁለት ቀናት የሚቆውን ጉባዔውን የውይይት አጀንዳዎችን እንዲሁም የ11ኛውን መደበኛ እና 6ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ መርምሮ በማጽደቅ መጀመሩን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ምክርቤቱ በዛሬ የጉባዔ ውሎው በርዕሰ-መስተዳድሩ የሚቀርበውን የክልሉ መንግስት የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም በማድመጥ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡






