መንግስት ለእንቦጭ ማስወገጃ በጀት በአፋጣኝ ካለቀቀ በቀጣዮቹ 2 ወራት አረሙ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚስፋፋ ተነገረ

0
584

የጣና ሃይቅና ሌሎች የዉሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ወቅቱ አረሙ የሚስፋፋበት ወቅት በመሆኑ የፌደራሉ እና የክልሉ መንግስት የበጀት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በቀጣዮቹ 2 ወራት አረሙ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚስፋፋ አስታውቋል።

በኤጀንሲዉ የብዝሓ ህይወት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ መዝገቡ ዳኘዉ በተያዘዉ ክረምት አረሙን ለማስወገድ የበጀት ችግር ገጥሞናል ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ.ኤም ተናግረዋል፡፡

አረሙ ከዚህ ወር ጀምሮ እስከ መስከረም ድረስ ባሉት 3 ወራት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚስፋፋ የገለፁት አቶ መዝገቡ፤ በእነዚህ ወራት ከፍተኛ ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል፡፡

በቅርቡ በተካሄደዉ አገር አቀፍ እንቦጮን የማስወገድ ዘመቻ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነዉን አረም ማስወገድ ቢቻልም አሁንም ክትትል እንደሚያስፈልገዉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ ባለዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ከበጀት ስጋቱ በተጨማሪ አርሶ አደሮችን ለማሰማራት ችግር እንደፈጠረም ተነስቷል፡፡

ህብረተሰቡ የክልሉና የፌደራሉ መንግስት በዚህ በክረምት ወቅት በሚከናወነዉ እንቦጭን የማስወገድ ስራ ላይ በትኩረት እንዲሳተፍም ጥሪ ቀርቧል፡፡

የእንቦጭ አረም በጣና ሃይቅ ዙሪያ በ30 ቀበሌዎች ከ4 ሺ ሄክታር በላይ የሚሆነዉን የሃይቁን ክፍል ተሸፍኖ የነበረ ሲሆን በዚህ አመት በተሰራዉ ስራ 90 በመቶ ማስወገድ መቻሉን የኢትዮ ኤፍ.ኤም ዘገባ አመላክቷል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here