ኢትዮጵያና ጃፓን የ120 ሚሊዮን ብር የእርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ

0
544

ኢትዮጵያና ጃፓን የ120 ሚሊዮን ብር የእርዳታ ስምምነት በገንዘብ ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ ስነ ስርአት ተፈራረሙ፡፡

በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ፕሮግራም ስር የሚካተተው ይህ የእርዳታ ስምምነት የሩዝ ሰብልን በማቅረብ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያግዝ ሲሆን በገበያው ውስጥ የሩዝ ሰብል አቅርቦትን በማሳደግ የሩዝ ፍለጎትን ለማሟላት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም እ.ኤ.አ በሚያዚያ ወር 2020 በ20 የበለጸጉ ሀገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች በተወሰነው መሰረት በኢትዮጵያና በጃፓን መካከል የእዳ ማራዘሚያ የመግባቢያ ሰነድም ተፈርሟል፡፡

የእርዳታ ስመምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ያስሚን ወሀበርቢ የፈረሙ ሲሆን በጃፓን በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ክብርት ኢቶ ታካቶ መፈረማቸው ታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here