ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከዳያስፖራው ማህበረሰብ በ72 ሰዓታት ከ90 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚደረግበት ድረ ገፅ www.mygerd.com ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ የውጪ ሀገራት ከሚኖሩ ከ742 ኢትዮጰያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እስከ ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ 91 ሺህ 395 ዶላር መሰብሰቡ ታውቋል።
በዚህ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ ላይም 39 ሰዎች ለልገሳው የሚሆን ዘመቻ በማድረግ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል።




