ለህዳሴው ግድብ በ72 ሰዓታት  ከ90 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ

0
744

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከዳያስፖራው ማህበረሰብ በ72 ሰዓታት  ከ90 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚደረግበት ድረ ገፅ www.mygerd.com ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ የውጪ ሀገራት ከሚኖሩ ከ742 ኢትዮጰያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እስከ ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ 91 ሺህ 395 ዶላር መሰብሰቡ ታውቋል።

በዚህ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ ላይም 39 ሰዎች ለልገሳው የሚሆን ዘመቻ በማድረግ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here