የህወሓት ሀይሎች በትግራይ ክልል ባሉ የኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት እንዲቆም የአሜሪካ መንግስት አሳሰበ

0
602

በትግራይ ክልል በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የህወሓት ታጣቂዎች እየፈጸሙት ያለው ጥቃት እንዲቆም የአሜሪካ መንግስት አሳስቧል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትናትናው እለት ባወጣው መግለጫ፤ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የህውሓት ኃይሎች በክልሉ በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ስለመሆኑ አሳማኝ መረጃዎች እንዳሉት አስታውቋል።

በተለይም በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የስደተኞች ካምፖች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ስለመሆናቸውም ገልጿል።

በክልሉ ያሉ የታጠቁ አካላት በኤርትራዊያን ስደተኞች፣ ጥገኝነት በጠየቁ አካላት፣ በሰብአዊ ድጋፍ ሰራተኞች እንዲሁም በግጭቱ ሳቢያ በተፈናቀሉ ግለሰቦች ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት እንዲያቆሙም ሚኒስትሩ በመግለጫው ጠይቋል፡፡

በክልሉ የኤርትራ ስደተኖች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ይህ የመጀመሪያ አለመሆኑን ያስታወሰው መግለጫው፤ ከዚህ ቀደም በጥር ወር ላይ በስደተኞቹ ላይ ግድያ ጨምሮ አፈና እና መሰል ጥቃቶች መፈፀማቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here