የቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የጤና ባለሞያዎች ኮቪድ 19ኝን ለመዋጋት ላበረከቱት አስተዋጾ የእውቅና እና ምስጋና መርሀ ግብር ተካሄደ።
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የሚሊኒየም ኮቪድ 19 ህክምና ማእከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ውለታው ጫኔ በእለቱ ባደረጉት ንግግር፤ ምስጋናው የትናንቱን ስራ ብቻ የሚያወሳ ሳይሆን የነገውን ሃላፊነታችንን የበለጠ የሚያመለክት መሆኑን በመገንዘብ ተገቢውን የስነልቦና ተያያዥ ዝግጅት ማድረግ አለብን ሲሉ አሳስበዋል።
ለዚህ ወረርሽኝ ምላሽ መላው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል ።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶከተር ዮሐንስ ጫላ መላው፤ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሰራተኞች ሆነው ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት ህይወት ሰጥተው ህይወታቸው ላለፈ የህክምና ባለሞያዎች ያላቸውን ክብር ገልጸዋል ።
የኮቪድ ወረርሽኝ ስጋት አሁንም መኖሩን ጠቁመው የህክምና ባለሞያዎች አሁን እያደረጉ ያሉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል ። ለዚህም የከተማው ጤና ቢሮ ሁሌም ከጎናቸው እንደሚቆም ተናግረዋል።
የጤና ሚንስቴር ሚኒስትር ድኤታ ወይዘሮ አለምፀሀይ ጳውሎስ በበኩላቸው የራሳቸውን ህይወት መስዋዕት አድርገው ሌሎችን ለታደጉ የህክምና ዘርፍ ባለሞያዎች ቤተሰቦች መፅናናትን መመኘታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
የተደረገው ምስጋና ስንቅ ሆኖም ከፊት የተደቀነውን የኮቪድ 19 ስጋት ለመቀልበስ የህክምና ባለሞያዎች እጅ ለእጅ መያያዝ እንዳለባቸው መናገራቸውም ታውቋል።






