ሕገ-ወጥ የጎዳና ላይ ማስታወቂያዎች የከተማዋን ውበት እያደበዘዙ ነው ተባለ

0
718

ሕገ-ወጥ የጎዳና ላይ ማስታወቂያዎች የከተማዋን ውበት እያበላሹ በመሆኑ በዚህ ድርጊት ላይ በሚሳተፉ አካለት ላይ የተጠናከረ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ደንብ ማስከበር ዘርፍ፣ የደንብ መተላለፍ ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ እንደተናገሩት ይህ ተግባር ከደንብ መተላለፍ ተግባር ውስጥ ፈታኝ የሆነ እና የከተማዋን ገፅታ እያበላሸ መሆኑን ጠቁመው፤ ባለፈው በጀት ዓመት በዘርፉ 1497 /አንድ ሺ አራት መቶ ሰጠና ሰባት/ እርምጃ ለመውሰድ ታቅዶ በ1296ቱ /አንድ ሺ ሁለት መቶ ዘጠና ስድስቱ/ ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ለመንገድ ላይ ማስታወቂያ ፍቃድ የሚሰጠው የግንባታ ፍቃድ ቢሮ ሲሆን ፍቃድ የሰጣቸውን አካላት በወቅቱ በግልባጭ ለደንብ ማስከበር ዘርፍ በአግባቡ ማሳወቅ እንዳለበት አስረድተዋል፡፡

አክለውም የግንባታ ፍቃድ ቢሮም በተመረጡ የከተማዋ ቦታዎች እና እንዲሁም ባስ እና ባቡር መጠበቂያ ስፍራዎች ላይ ደረጃቸውን የጠበቁ የማስታወቂያ ሰሌዳዎችን በማዘጋጀት ሕጋዊነታቸውን በጠበቀ መልኩ ማስተናገድ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ የደንብ ማስከበር ዘርፉ ደንቦችንና መመሪያዎች እየተስተካከሉ ሲሄዱ አብዛኛዎቹን ሁለት ቦታ ሆነው አላሰራ ያሉ ደንብና መመሪያ ክፍተቶችን በማረም ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመናበብ በስምምነት ሰነድ ተሳስረው በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ይህን ተግባር የሚፈጽሙ አካላት የከተማዋን ውበት እና ገፅታ በከፍተኛ ሁኔታ እያጠለሹ በመሆናቸው ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡና ሕብረተሰቡም እነዚህን አካላት በመገሰጽ ከተቋሙ ጎን እንዲሰለፍ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን ከቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here