የሰላም ሚኒስትሯ ከተመድ የፖለቲካና ሰላም ግንባታ ጉዳዮች ዋና ፀሀፊ ጋር ተወያዩ

0
704

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት የፖለቲካና ሰላም ግንባታ ጉዳዮች ዋና ፀሀፊ ዶክተር ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በውይይቱ በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች በተለይም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከአንድ ወገን የተኩስ አቁም ስምምነት በኋላ ስላለው የሰብዓዊ እርዳታን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ሀገራችን ስለምትገኝበት የለውጥ ሂደት፣ በቅርቡ ያካሄድነው ሀገራዊ ሰላማዊ የምርጫ ሂደት እና በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ላለፈው አንድ አመት በመካሄድ ላይ ስላለው ሁሉን አቀፍ የማህበረሰብ የምክክር ሂደትን አስመልክቶ ገለጻ መደረጉንም አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here