በ5000 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ አለፉ

0
985
በቶኪዮ ኦሎምፒክ በሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ በሁለት ምድቦች ተደልድለው ውድድራቸውን ያደረጉት ጉዳፍ ፀጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬና ሰንበሬ ተፈሪ የፊታችን ሰኞ ለሚካሄደው የፍፃሜ ውድድር አልፈዋል::

በውድድሩም ከመጀመሪያ ምድብ ሰንበሬ ተፈሪ 14:18 31 በመግባት 3ኛ፣ እጅጋየሁ ታዬ ደግሞ 14:48 52 በመግባት 4ኛ ሆነው ማጣሪያውን አልፈዋል::
ከሁለተኛው ምድብ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 1ኛ ደረጃ በመያዝ ማጣሪያውን አልፋለች፡፡
ኢትዮጵያ በቶኪዮ 2020 የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ልታሸንፍ የምትችልበት የወንዶች 10,000 ሜትር ፍፃሜ ከደቂቃዎች በኋላ ይካሄዳል::

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here