በሕወሓት ቡድን የተገደሉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን የሚያስብ የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት ነገ ይካሄዳል ተባለ

0
598
በኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት በተፈረጀው በሕወሓት ቡድን የተገደሉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን የሚያስብ የትግራይ ተወላጆች የሚሳተፉበት የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት ነገ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለፀ።
ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ጋዜጠኛ አርዓያ ተስፋማሪያም የሻማ ማብራትና የጸሎት ስነ-ስርዓቱን አስመልከቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጋዜጠኛ አረዓያ እንደተናገሩት፤ 53 የትግራይ ተወላጆች በቀናነት ሕዝባቸውን ለማገልገል በስራ ላይ ተሰማርተው በአሸባሪው ተገድለዋል።
በነገው እለትም የትግራይ ተወላጆችና ወዳጆች በተገኙበት እነዚህን ንጹሃን የሚያስብ የሻማ ማብራትና የጸሎት ፕሮግራም ይካሄዳል ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።
ከመታሰቢያ መርሃ ግብሩ በኋላም በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት በኩል የእነዚህ ንጹሃን ሁኔታ እንዲከታተል መልዕክት እንደሚተላለፍ ጋዜጠኛ አርዓያ ተናግሯል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here