የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ውስጥ የበረራ አገልግሎቱን በ30 በመቶ አሳደገ

Views: 1133

የስካይ ትራክ ባለ 4 ኮኮብ ደረጃ ባለቤት የሆነው ኢትዮጵያ አየር መንገደድ በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ተለያዩ አካባዎች የሚያደርገውን የበረራ አገልግሎት በ30 በመቶ ማሳደግ እንደቻለ አስታወቀ። አየር መንገዱ በአገር ውስጥ ያሉትን መዳረሻዎቹን በመጨመር፣ የበረራ ብዛቶቹን በማሳደግ እንዲሁም አየር ማረፊያዎቹንም በማዘመን የአገልግሎት አቅሙን ማሳደግ እንደቻለ ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ 22 መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን በቀን 51 በረራዎችን እና በሳምንት ደግሞ ከ350 በላይ በረራዎችን ወደ እነዚሁ መዳረሻዎቹ እንደሚያደርግ በመግለጫው ተጠቅሷል። የአገልግሎት አሰጣጡን በይበልጥ እያጠናከረ የሚገኘው አየር መንገዱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተደገፈው የደንበኞች አገልግሎት በበጀት ዓመቱ 2ነጥብ8 ሚሊየን ለሚሆኑ የሀገር ውስጥ መንገደኞች የአየር ትራንስፖርት አገልግሎትን ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በአገር ውስጥ ባሉት መዳረሻቹ አገልግቶችን በመስጠት ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን እና ትስስሩን ለማጎልበት እየሰራ እንደሚገኝ የሚገልጸው አየር መንገዱ በአፍሪካ በአገር ውስጥ በተመጣጣኝ ክፍያ አገልግት የሚሰጥ አየር መንገድ እንደሆነም በመግለጫው አውስቷል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com