ኢትዮጵያ ወደ ሌሎች ሀገሮች የሸሹ ሀብቶችን ለማስመለስ ሕጋዊ መሰረት እንዳላት ተገለፀ

0
605

ኢትዮጵያ በሙስናና ብልሹ አሰራሮች ወደ ሌሎች አገሮች የሸሹ ሀብት ለማስመለስ ሕጋዊ መሰረት እንዳላት በሀገራችን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን (UNCAC) አፈጻጸም ሪፖርት ገምጋሚ ኮሚቴ ገለፀ፡፡

በሪፖርት ግምገማው ላይ እንደተገለፀው በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ወይም ሌላ የፍትህ አካል የሀገሪቱ ሀብት በሙስና ተመዝብሯል ተብሎ መረጃ ካለ እና አለበት ከሚባለው ሀገር መረጃ በማቅረብ እንደየሁኔታው እንዲመልስ ለማድረግ ሕጋዊ መሰረት አላት፡፡

ይህም በፀረ-ሙስና አዋጅ 881/2015 እና በፋይናንስ ደህነት መረጃ ማዕከል ማቋቋሚያ አዋጅ 780/2013 መሰረት በሙስና ወንጀል የተገኘ ሀብት እንደሚወረስ ገልጾ ሀብት ለማስመለስ አለማቀፋዊና ህጋዊ ተቀባይነት እንዳለው ኮሚቴው አብራርቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሀገሪቱ በሙስና ወንጀል የተገኘን ገንዘብና ወንጀለኛን አሳልፎ የመስጠት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀረ-ሙስና ኮንቨንሽን አንቀጽ 44 ታዓቅቦዋን ማንሳቷ ሀብቱና ወንጀለኛው ለሀገሪቱ እንደሚመለስ በኮሚቴው ተብራርቷል፡፡

ይህን መሰረት በማድርግ ሀገሪቱ ከአሁን በፊት በሙስና የሸሸባትን ሀብት ከሀገሮች ጋር ያላትን ህጋዊና ዲፕሎማሲያዊ ቅርበት በመጠቀም ለማስመለስ እየጠየቀች መሆኑን የኮሚቴው አባላት በውይይቱ አንስተዋል፡፡

ከፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከጠቅላይ ዓቃቤ ህግ፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል የተውጣቱ የብሔራዊ ኮሚቴ አባላት ለሶስት ቀናት ሲያካሄዱት የነበረው የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ የተጠናቀቀ ሲሆን በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦች ከተካተቱ በኋላ ድጋሜ ታይቶ ለሲቪክ ማህበራት እንደሚቀርብም መገለፁን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here