ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው 80 ታወሮች መዘረፉን በኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል ደቡብ ሪጅን አስታወቀ

0
851

እያንዳንዳቸው1.8 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው 80 ታወሮች እንደተዘረፉበት በኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል ደቡብ ሪጅን አስታወቀ።
በዚህም ምክንያት በምዕራብ አርሲ ዞን ተደጋጋሚ የመብራት መቆራረጥ እያጋጠመ እንደሆነ ተነግሯል። እንደ ሪጅኑ ገለጻ ከሆነ ከፍተኛ ዝርፊያ የሚፈጸምባቸው በዞኑ የሻሸመኔ እና ወንዶ ወረዳዎች በ2013 በጀት ዓመት በስርቆት ምክንያት ስምንት ታወሮች ወድቀዋል።
ይህም ዞኑ ከገናሌ ዳዋ የሚመጣውን ኃይል እንዳያገኝ እንከን እንደሆነበት የሪጅኑ የኃይል ስርጭት ማዕከላት ኦፕሬሽንና ጥገና ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል። ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ ብረቶቹ በውጭ አገር ገበያ የአንዱ ዋጋ 1.8 ሚሊዮን ብር እንደሚገዛ የገለጹት አቶ አለማየሁ፣ ሕብረተሰቡ በኃይል እጦት እንዳይቸገር የተዘረፉ ታወሮችን በእንጨት የመተካት ሥራ እየተሠራ ቆይቷል ብለዋል።
በዚህም በየዓመቱ ከ 3.1ሚሊዮን ብር በላይ ድርጅቱ ወጪ እንዲያደርግ አስገድዶታል። የደቡብ ሪጅን ኤሌክትሪክ ኃይል ስርጭት ጥገና ኃላፊ አቶ ሞሲሳ ገልቻ በበኩላቸው ከሀላባ ሻሸመኔ ካሉ 230 ታወሮች ውስጥ 80 ያህሉ ዝርፊያ ተፈጽሞባቸዋል ብለዋል። በዋጋ ሲተመኑም 144 ሚሊየን ያወጣሉ።
የሻሸመኔ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አወል ዋፎ ድርጅቱ በወረዳው ላይ ላቀረበው ቅሬታ ቅድሚያ ታወሮቹ ተሟልተው ስለመገጠማቸው ማረጋገጫ የለኝም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ተቋሙ አመታትን በዘለቀው የታወር ዝርፊያ የማስፋፊያ ሥራ ከመሥራት ይልቅ የተዘረፈውን በመተካት እየተጎዳ ነው ያሉት አቶ አለማየሁ፣ የፌደራል መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 144 ነሐሴ 1 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here