በሕጻፅና ሽመልባ መጠለያ ለነበሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ምዝገባ እየተደረገላቸው ነው ተባለ

0
487

በትግራይ ክልል ሕጻፅ እና ሽመልባ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የነበሩ የኤርትራ ስደተኞች በአዲስ አበባ መኖር እንዲችሉ የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ከስደተኞች እና ከስደት ተመላሽ አስተዳደር ኤጄንሲ ጋር በመሆን ምዝገባ እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል።
ኤርትራዊያኑ በሕጻፅ እና ሽመልባ መጠለያ ጣቢያ በነበሩበት ወቅት በአሸባሪው ሕወሓት ግድያን ጨምሮ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈፅምባቸው እንደነበር በዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን በሰፊው ሲዘገብ የቆየ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል።
በአዲስ አበባ ምዝገባ ለሚደረግላቸው ኤርትራዊያን ለሦስት ዓመት የሚያገለግል መታወቂያ በማዘጋጀት በአዲስ አበባ እንዲኖሩ የሚያስችል ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ስደተኞቹ ከመጠለያ ወጥተው ኮሚሽኑ በንግድ ባንክ በኩል በሚያደርሳቸው ክፍያ የግላቸውን ሕይወት እንደሚመሩ ተመላክቷል።


ቅጽ 3 ቁጥር 144 ነሐሴ 1 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here