ክብረ ንፅህና ተይዞ አረብ ሀገር መሄድ አይቻልም በማለት ታዳጊዎችን የደፈረው ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ

0
903

ክብረ ንፅህናችሁን ይዛችሁ አረብ ሀገር መሄድ አይፈቀድም በማለት ሁለት ታዳጊዎችን በማታለልና በማስፈራራት የደፈረው ግለሰብ በ20 ዓመት እስራትና በገንዘብ መቀጣቱን ፖሊስ አስታወቀ::

ወንጀሉን የተባበረችው ባለቤቱም በ10 ዓመት እስራትና በገንዘብ መቀጣቷም ተገልጿል

የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ራዲያ ቱራ ለኢዜአ እንደገለፁት ግለሰቡ “ታዳጊዎች ልጃገረድ ሆነው አረብ ሀገር መሄድ አይፈቀድላቸውም” በማለት አታሎና አስፈራርቶ መድፈሩን ገልጸዋል።

ተከሳሽ ሙስጠፋ ከድር ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓም በአዳማ ከተማ ሚግራ መናኸሪያ አካባቢ በሚገኝ ሰላም መኝታ ቤት አልጋ ይዞላቸው ምሽት አራት ሰዓት ላይ ታዳጊዎቹን መድፈሩን ዋና ኢንስፔክተሯ ተናግረዋል።

የታዳጊዎቹ ዕድሜ 14 እና 15 ዓመት መሆኑን የገለጹት ዋና ኢንስፔክተር ራዲያ፤ ከአርሲ ዞን ዲገሉና ጥዮ ወረዳ ከቤተሰቦቻቸው ጠፍተው በአሰላ ከተማ መገኘታቸውን ገልፀዋል።

የተከሳሽ ባለቤት ሰዓዳ ወይንም በቅፅል ስሟ ቢፍቱ ሙሐመድ የተባለች ግለሰብ ግንቦት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ታዳጊዎችን አረብ ሀገር እልካቸዋለሁ በማለት ከአሰላ ወደ አዳማ እንዳመጣቻቸው ዋና ኢንስፔክተር ራዲያ አመልክተዋል ።

በማግስቱ ግለሰቡ ለራሱና ለባለቤቱ አንድ መኝታ እንዲሁም ለሁለቱ ታዳጊ ሴቶች አንድ መኝታ ቤት በመከራየት ምሽት አራት ሰዓት በጩቤ አስፈራርቶ መድፈሩን በሰውና በሰነድ ማስረጃ መረጋገጡን ተናግረዋል።

የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባዋለው ችሎት 1ኛተከሳሽ ሙስጠፋ ከድር በ20 ዓመት እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ መወሰኑን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ 2ኛ ተከሳሽና የወንጀሉ ተባባሪ የሆነችው ባለቤቱ ሰዓዳ ሙሐመድ በ10 ዓመት እስራትና በገንዘብ እንድተቀጣ ውሳኔ መስጠቱን ዋና ኢንስፔርተር ራዲያ ቱራ አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here