ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅን ጨምሮ አራት ኢትዮጵያውያን ከተፅዕኖ ፈጣሪ 100 አፍሪካውያን ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

0
645

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ አራት ኢትዮጵያውያን ከስኬታማና ተፅዕኖ ፈጣሪ 100 አፍሪካውያን ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ።
በዝርዝሩ ውስጥ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅን ጨምሮ የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና የሶል ሬብልስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤተልሄም ጥላሁን መካተት ችለዋል። ዝርዝሩን ያወጣው አቫንስ ሚዲያ (100women.avancemedia.org) የተሰኘ ድርጅት ሲሆን በየዓመቱ ስኬታማና ውጤታማ የሆኑ 100 የአፍሪካ ሴቶችን ስም ዝርዝር በማውጣት ይታወቃል።
በድርጅቱ ዝርዝር ለመካተት የአመራርና አፈጻጸም ክህሎት፣ በግል ያስመዘገቡት ስኬት፣ እውቀት ማጋራት እና የማይመቹ አሠራሮችን መቀየር የሚሉት መስፈርቶች ዋና ዋና መሆናቸውን ከድርጅቱ ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ይጠቅሳል።


ቅጽ 3 ቁጥር 148 ነሐሴ 29 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here