የከተማ አውቶብሶቹን ከማዕከል ሆኖ መቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ ሊገጠም ነው

0
686

ስምሪት የወጡ አውቶቡሶቹን ከማዕከል ሆኖ መቆጣጠር የሚያስችል የቴክኖሎጂ መከታተያ ለመግጠም ዝግጅት ማጠናቀቁን አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።
መከታተያው አውቶብሶቹ ያሉበትን መስመር ለማወቅ፣ ረጅም ጊዜ ያለ ሥራ እንዳይቆሙ እና የምልልስ ፍጥነቱን ለማስተካከል እንደሚያግዝ አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል። ከሰሞኑ በመስመር ቁጥር 30 አውቶብስ ላይ አላግባብ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል በሚል ለቀረበው ቅሬታም፣ ከዛሬ ጀምሮ በመስመሩ ላይ የታሪፍ ማስተካከያ በማድረግ ከ8 ብር እስከ 5 ብር እንደ ርቀቱ ተሳፋሪዎች እንዲጠቀሙ ይደረጋል ተብሏል። ከነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ መንገድ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ባወጣው ታሪፍ አገልግሎቱ እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል።
በቀጣይ ዓመት ተማሪ ስለሚኖር የትራንስፖርት ተጠቃሚው ቁጥር ስለሚጨምር፣ ይህን ታሳቢ በማድረግ በተለያየ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የቆሙ አውቶብሶችን ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብሏል። ድርጅቱ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በ125 መደበኛ እና በ10 ልዩ መስመሮች የብዙኀን ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተጠቁሟል።


ቅጽ 3 ቁጥር 148 ነሐሴ 29 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here