በአዲስ አበባ ዛሬ በደረሰ ድንገተኛ የእሳት አደጋ 5 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ

0
646
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ክላስተር 04 በተለምዶ ጃክሮስ አደባባይ አካባቢ የሚገኘው ቤላ ፒዛ (BELLA PIZZA) ድንገት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ አደጋ እንደደረሰበት የሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ተካ ወ/ጊዎርጊስ ገልፀዋል።
ሃላፊው በገለፃቸው የእሳት አደጋው ከምግብ መስሪያ ማድቤት ውስጥ በሚገኝ የጋዝ ሲሊንደር ድንገተኛ መፈንዳት የተነሳ መሆኑን ጠቁመው በአደጋው አምስት የድርጅቱ ሰራተኞች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።
አደጋው ከዚህ የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስ ከእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር የቦሌና የአራዳ ቅርንጫፍ ጋር በመሆን ከፍተኛ ስራ በመስራት የአደጋውን መጠን መቀነስ መቻሉን ተካ ጠቁመዋል።
ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ለህክምና ወደ ካዲስኮ ሆስፒታል መላካቸውንና በድርጅቱ የወደመው ንብረት ግምት እየተጣራ መሆኑንም ሃላፊው ጨምረው ገልፀዋል ሲል የወረዳ 07 ፕሬስ በማህበራዊ ድረ ገፁ አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here