በኢትዮጵያ በእብድ ውሻ በሽታ በዓመት ከ2 ሺህ 700 በላይ ሰዎች ህይወታቸዉን እንደሚያጡ ተገለጸ:-ይህም ቁጥር ከአፍሪካ ከፍተኛው መሆኑም ተነግሯል

0
997

በኢትዮጵያ የእብድ ዉሻ በሽታ ቀላል የማይባል ጉዳቶች እያስከተለ መሆኑን በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የእንስሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ቡድን መሪ ዶክተር ይመር ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይ ባለው አሀዛዊ መረጃ መሰረት በኢትዮጲያ በዓመት 2 ሺህ 700 ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ ህይወታቸዉን እንደሚያጡ ቢገለጽም ቁጥሩ ከዚህም ሊልቅ እንደሚችል ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡

የእብድ ውሻ በሽታ በበሽታው በተለከፉ እንስሳት ንክሻ ከውሻ፣ ድመት፣ ቀበሮ፣ ተኩላና ሌሎች ወደ ጤናማ ሰው ሊተላለፍ የሚችል አደገኛ በሽታ ሲሆን ከሰዉ ወደ ሰው ሊተላለፍ የሚችልበት መንገድ ሰፊ መሆኑን ዶክተር ይመር ተናግረዋል፡፡

በበሽታው የተያዙ ሰዎች ምልክቶቹ መታየት የሚጀምሩት የአለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው ገደብ መሰረት ከአንድ እስከ ሶሥት ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ቢሆንም አሁን በሚታዩ መረጃዎች ይህ የጊዜ ገደብ ከሳምንት ባነሰ እና ከአመት በበለጠ ጊዜ ሊለያይ ይችላል፡፡

የጊዜ ገደቡ የሚወሰነው የበሽታ አምጭ ረቂቅ ህዋስ ወደ ማዕከላዊ የነርቭ ስርዓት ለመድረስ የሚፈጅበት ርቀት ሲሆን በአንገት፣ በጆሮ እና በትከሻ አካባቢ ከተነከሰ በአጭር ጊዜ ምልክቱ ሊጀምር ይችላል፡፡

ከተነከሰበት ቦታ በተጨማሪ የተነከሰበት መጠንም ለዚህ ምክንያት ይሆናል፡፡ ምልክቶቹ ሰዎችን እስከመናከስ ሊያደርስ ይችላል ተብሏል፡፡

በሽታው ላለባቸው ሰዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁለት ዓይነት መድኃኒት ይሰጣል፡፡ በኢትዮጲያ በዋጋ ዝቅ የሚለው እና ለ18 ቀናት በእንብርት የሚሰጠው ሲሆን ለ3 ቀናት በክንድ የሚሰጠው ክትባት ውድ በመሆኑ በኢትዮጲያ እየተሰጠ አይደለም ሲል ለብስራት ሬድዮ ዘግቧል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here