ህፃን ልጁ ላይ የግብረሰዶም ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

0
542
የራሱ ህፃን ልጅ ላይ የግብረሰዶም ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡

ተከሳሽ በጥቅምት እና ህዳር ወር 2011 ዓ.ም በተለያዩ ቀናት ልዩ ቦታዉ ኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ዉስጥ ዕድሜዉ 7 ዓመት የሆነዉ የራሱ ልጅ ላይ የግብረሰዶም ጥቃት ወንጀል የፈፀመበት በመሆኑ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ወንጀል ችሎት በአቃቤ ህግ ክስ ቀርቦበታል፡፡

ተከሳሽ በችሎት ቀርቦ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዶ ተከራክሯል፡፡

የዓቃቤ ህግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ቀርበው ተከሳሽ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ እንደክስ አመሰራረቱ ያስረዱ በመሆኑ እንዲከላከል ችሎቱ ብይን ቢሰጥም፤ተከሳሽ ባቀረባቸዉ የሰነድና የሰዉ መከላከያ ማስረጃዎች መከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ መዝገቡን መርምሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቶ ነበር ለመስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዞ መዝገቡ ያደረው፡፡

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ከላይ በተገለጸው እለት በዋለው ችሎት ተከሳሽ በአስራ ስድስት (16) ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከየኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here