ለስድስት ኩባንያዎች የከፍተኛ ማዕድን ምርት ፈቃድ መሰጠቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ኩባንያዎቹ ፈቃድ የተሰጣቸው የማዕድን ፍለጋውን አጠናቀውና አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማሟላት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚህም ኩርሙክ ጎልድ ማይን ፣ኢትኖ ማይኒንግ እና ኦሮሚያ ማይኒንግ ኩባንያዎች የወርቅ ምርት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡
እንዲሁም አሊ ሀሚል ካሐዲም የብሮሚን እና ክሎሪን ምርት ፈቃድ ሲወስድ፣ ኪሪፕቶ ማይኒንግ ኤንድ ኬሚካልስ እና ቡሁሚ ማይኒንግ ኩባንያዎች ደግሞ የእምነበረድ ምርት ፈቃድ መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡
ስምምነቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የኩባንያዎቹ ስራ አስኪያዎች ተፈራርመዋል፡፡
ኩባንያዎቹ ከ4 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ካፒታል ያስመዘገቡ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን፤ ከ1 ሺህ 300 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩን ከማዕድና ነዳጅ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n







