‹‹ላገዛችሁኝና ሳጠፋ ለነቀፋችሁኝ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ›› አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር

0
618

ተሰናባቹ የአማራ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ‹‹ላገዛችሁኝና ሳጠፋ ለነቀፋችሁኝ ሁሉ›› ምስጋናዬን አቀርባለሁ›› ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር ረፋዱን በተዋቀረው አዲሱ የአማራ ክልላዊ መንግሥት ከነበሩበት ኃላፊነት መነሳታቸውና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ በነበሩት ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት መተካታቸው ይታወቃል፡፡

ሹም ሽሩን ተከትሎም ‹‹ከ2011 ሰኔ ጀምሮ በክልሉ የተሰጠኝን ከባድ ኃላፊነት እንድወጣ ከጎኔ ሆናችሁ ላገዛችሁኝ ሳጠፋ ለነቀፋችሁኝ ሁሉ ምስጋናየን አቀርባለሁ። ለሁሉም ነገር ፈጣሪን አመሰግናለሁ። ለተተኪ ጓደኞቸ መልካም የስራና የትግል ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ›› ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here