የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም የተለየያዩ አገራት መሪዎች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚከናወነውን የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በዓለ ሲመትን ለመታደም የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃን ሚኬል ሳማ ሉኮንዴ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልቫኪር ማያርዲት፣ የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ እንዲሁም የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ረፋዱን አዲስ አበባ ገብተዋል።
መሪዎቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።




