በቦረናና አካባቢው በተከሰተ ድርቅ የዱር እንስሳት በውኃ ዕጥረት ለአደጋ መጋለጣቸው ተነግሯል

0
657

የቦረና ብሔራዊ ፓርክን መገኛ ጨምሮ በቀጠናው በተከሰተ ድርቅ ምክንያት የዱር እንስሳቱ የሚመገቡት እና የሚጠጡት ውኃ ከቤት እንስሳት ጋር በመጋራታቸው ዕጥረት ተከስቷል ተብሏል።
በዚህም ፓርኩ የቤት እንስሳቱ በቀን እንዲጠጡ እና ሌሊቱን ደግሞ የዱር እንስሳቱ ሳይረበሹ ውኃ የሚያገኙበትን አማራጭ እየተከተለ እንደሆነ ገልጿል።
ገረኑክ፣ የቆላ አጋዘን፣ የሜዳ ፍየሎች፣ ሰጎን እና የበርካታ አእዋፍት መገኛ የሆነው የቦረና ብሔራዊ ፓርክ፣ በኢትዮጵያ የትልቁ የሜዳ አህያ (Gravy’s Zebra) ኹለተኛው ወሳኝ ቀጣና መሆኑ ይታወቃል፡፡
በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ በርካታ ዜጎች ችግር ላይ መውደቃቸው፤ በርካታ እንስሳትም መሞታቸው፤ አሁንም አደጋ ላይ ያሉ መኖራቸው ከዚህ ቀደም የተገለጸ መሆኑ አይዘነጋም።
በድርቅ ምክንያት ችግር ለገጠማቸው ወገኖች ለመድረስ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት፣ በአገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ዜጎች ርብርብ እያደረጉ መሆኑም ተነግሯል፡፡


ቅጽ 3 ቁጥር 156 ጥቅምት 20 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here