የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ወደ አገር ውስጥ ገብቷል ተባለ

0
768

የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ተብሎ 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ወደ አገር ውስጥ መግባቱን የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታውቋል፡፡
የንግድ ሥራ ኮርፖሬሽኑ አሰታውቋል እንደተባለው ከሆነ፣ በመጀመሪያ ዙር የገባው 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ፣ የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ከታቀደው 8 ሚሊየን ኩንታል ውስጥ መሆኑን ነው መረዳት የተቻለው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ቀሪው 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ በሚቀጥሉት 15 ቀናት ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቻ ደምሴ መግለጻቸውም ተሰምቷል።
ዘገባው እንደሚያመላክተው ከሆነ፣ ምርቱ በአዳማ፣ በሻሸመኔ፣ በባህር ዳር፣ በድሬዳዋ እና አዲስ አበባ በሚገኙ የኮርፖሬሽኑ አምስት ማዕከላት እንደሚሠራጭም ተብራርቷል።
ሥርጭቱ በሚቀጥሉት 15 ቀናት በተጠቀሱት ማዕከላት እንደሚከናወን እና የሚገባው ቦታ መድረሱን የሚከታተል ኮሚቴ ተዋቅሮ ቁጥጥር እንደሚደረግም ተጠቁሟል።
11 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የስንዴ ምርት በዳቦ ቤቶች ላይ የሚታየውን የዋጋ ጭማሪ እና የዱቄት ዕጥረት ለመቅረፍ ሚናው የጎላ ነው መባሉም ተጠቁሟል።
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን በመደገፍ በአገሪቷ ላይ የተቃጣውን የኢኮኖሚ ጦርነት ለመመከት እንደሚረዳም በዘገባው ተብራርቷል።
በተመሳሳይ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕብረተሰቡ ለማድረስ ኮርፖሬሽኑ ከአጋር አካላት ጋር እየሠራ እንደሆነና በቅርቡ ምላሽ እንደሚያገኝ መግለጹ ተዘግቧል፡፡


ቅጽ 4 ቁጥር 161 ሕዳር 25 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here