የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ናዛት ካን፣ ለሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባላት ፣ ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባቼሌት ግልጽ ደብዳቤ ፅፏል።
ኢሰመኮ በጻፈው ደብዳቤ፥ በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል እስከ ፈረንጆቹ ህዳር 3/2021 ድረስ የተፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በሌላ አካል በድጋሚ እንዲጣራ ማድረግ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት እና በኢትጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጥምረት የተካሄደውን ምርመራ እውቅና መንፈግ ነው ብሏል፡፡
ኮሚሽኑ ምርመራ ተደርጎ በሪፖርት የቀረበውን ጉዳት በሌላ አካል ከማስደገምና ሂደቱን ከማጓተት፣ ቀደም ብሎ በወጣው የምርመራ ሪፖርት መሰረት ተጎጂዎች እንዲያገግሙ፣ ወደ ተፈናቀሉበት ቦታ እንዲመለሱ እንዲሁም እንዲካሱ ብሎም ወንጀል የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ መሠራት ነበረበት ብሏል።
ኮሚሽኑ ሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እንደገና ይጣራ ከተባለ አጥፊዎቹ አካላት የፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመካድና እና ኮሚሽኑ የሰራውን ምርመራ ለማጣጣል ብሎም የኮሚሽኑን ተግባር ዝቅ የሚያደርግ ይሆናል ሲል ስጋቱን ገልጿል።
ቅጽ 4 ቁጥር 163 ታኅሣሥ 9 2014


