10 ምርጥና ንጹኅ አካባቢ ያላቸው

0
635

ምንጭ፤ ኢምግራንት ኢንቨስት (2021)

የቴክኖሎጂ እየተሻሻለ መምጣት ሥራዎችን ለማቀለልና ጉልበትን ለመቆጠብ ቀላል የማይባል ሚና ይጫወታል። ይሁን እንጅ እያንዳንዱ ቁስ ሲፈበረክና ጥቅም ላይ ሲውል ጥሩ ጎን ቢኖረውም መጥፎ ጎንም እንዳለው ይታወቃል። ከእነዚህም መካከል በኢንዱስትሪ መስፋፋት ብዙ ጥቅሞች ቢገኙም፣ በሌላ ጎን ከኢንዱስትሪው የሚለቀቁ በካይ ጭሶች አካባቢን ይበክላሉ።

ኢምግራንት ኢንቨስት የተሰኘው ድረ ገጽ በ2021 ባወጣው መረጃ መሠረት ከላይ የተዘረዘሩት አገራት ኬሚካል አካባቢያቸውን ሳያቆሽሽ በተሳካ መልኩ የሚያስወግዱ ናቸው ብሏል። በዚህም ዴንማርክ በዓለም ላይ ካሉት አገራት ምርጥ የፍሳሽ ማጣሪያ ሥርዓትን በመከተል 82.5 በመቶኛ ውጤት በማስመዝገብ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዛለች።

በመቀጠልም ስዊዘርላንድ እና ብሪታንያ ንጹኅ የመጠጥ ውኃ በማግኘት ግንባር ቀደም ሲሆኑ፣ ዜጎቻቸው ከፍተኛ የግል ንጽኅና አጠባበቅ እንደሚከተሉ ማወቅ ተችሏል። ከላይ ከተዘረዘሩት አገራት መካከል በዐስረኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ጀርመን የንጸኅና ደረጃዋ 77.2 በመቶኛ ነው ተብሏል።


ቅጽ 4 ቁጥር 167 ጥር 7 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here