በአብየ ግዛት የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የመተካቱ ሂደት በቀጣይ ወር እንደሚጀምር ተመድ አስታወቀ

0
666

አርብ ጥር 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአብየ ሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል የተመተካቱ ሂደት በቀጣይ ወር እንደሚጀመር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የሰላም ማስከበር ዘመቻ ኃላፊ ጅን ፔሬ ላክሮክስ አስታወቁ፡፡

ሱዳን በአብየ ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ ጥያቄ አቅርባ የነበረ ሲሆን፤ ጥያቄዋም በተመድ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል፡፡

ሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ይወጣ ያለችው በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል በድንበር ጉዳይ አለመግባባት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ኃላፊዋ ላክሮክስ ይህን ያሉት ከሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ም/ቤት ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ባደረጉት የስልክ ወይይት ነው ተብሏል፡፡

የሽግግር ም/ቤቱ እንደገለጸው አልቡርሃን ከተመድ ኃላፊ ጋር ያደረጉት ውይይት የተመድ ኢንትሪም ሴኩሪቲ ፎርስ ፎረ አብየ ውስጥ ያሉት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን በሱዳን መንግስት በተጠየቀው መሰረት ለመተካት የመከረ ነበር፡፡

በስልክ ወይይቱ ወቅት ላክሮክስ የመተካቱና የመተካቱ ስራ በፈረንጆቹ ቀጣይ የካቲት ወር እንደሚጀመርና እስከ ፈረንጆቹ መጋቢት 2022 እንደሚገጥል ማረጋገጣቸው ተዘግቧል ሲል አል አይን በድህረ ገጹ አስነብቧል፡፡

የተመድ የጸጥታው ም/ቤት ሰላም አስከባሪ ወደ አብየ ግዛት የሰላም አስካሪ የላከው፤ በነዳጅ በበለጸገችው አብየ ግዛት የሱዳንና የደበብ ሱዳን ጦሮች መፋጠጣቸውን ተከትሎ ነበር፡፡

_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here