አርብ ጥር 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሆስፒታል ሲደረግላቸው የነበረውን ህክምና ጨርሰው በሙሉ ጤንነት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ በሰላም ተመልሰዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 6 በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ ቅዱስነታቸው ፥ በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ጉባኤው ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ማስታወቁ ይታወሳል።
የኢ.ኦ.ተ.ቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያም ቅዱስ ፓትርያርኩ ሲደረግላቸው የነበረውን የህክምና ክትትል ጨርሰው በሙሉ ጤንነት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ መመለሳቸውን አስታውቋል።
_____________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



