10 ግዙፍ በዓለማችን የሚገኙ ግድቦች

0
1108

ምንጭ፤ ዊ – ዲጅታል መጋዚን (2021)

ዊ-ዲጂታል መጋዚን ተሰኘው ድረ – ገጽ በ2021 ይፋ ባደረገው መሰረት ከላይ የተዘረዘሩት በዓለማችን ውስጥ የሚገኙ ታላላቅ ግድቦች ናቸው።
በዚህም በዛምቢያ እና በዚምባብዌ መካከል ባለው የዛምቤዚ ወንዝ ላይ የተገነባውና 128 ሜትር ቁመት እንዲሁም 579 ሜትር ርዝመት ያለው ካሪባ ግድብ 185 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን፤ በዚህም የመጀመሪያውን ደረጃ ይዟል።
በመረጃው መሰረት ከካሪባ ቀጥሎ በዓለም ላይ ሁለተኛው ትልቁ ግድብ በ1954 እና 1964 የተገነባውና በሩሲያ ውስጥ የሚገኘው ብራትስክ የተሰኘው ግድብ ሲሆን፤ 169 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የሚይዝ፤ የ5.4 ካሬ ኪ.ሜ ስፋትና 125 ሜትር ቁመት ያለው መሆኑን ማወቅ ተችሏል።
ከእነዚህም በመቀጠል በ1961 እና 1965 በጋና ደቡብ ምስራቅ ከቮልታ ሀይቅ ጀርባ ተገንብቶ 144 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በማጠራቀም 660 ሜትር ርዝመት ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያው ጋና፤ ቤኒን እና ቶጎን የሚያገለግለው አኮሶምቦ ግድብ የሶሥተኛውን ደረጃ ይዞ ይገኛል።


ቅጽ 4 ቁጥር 169 ጥር 21 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here