ባልደራስ እና መኢአድ ዛሬ ጥምረት ለመመስረት  ይፈራረማሉ

Views: 330

 

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ(ባልደራስ) ዛሬ የካቲት27/2012 ቅንጅት ለመመስረት እንደሚፈራረሙ የባልደራስ ፕሬዚዳንት እስክንድር ነጋ ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ።

ከፊርማው በኋላም አስፈላጊውን መሰፈርት በሟሟላት ለመጪው ምርጫ በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚንቀሳቀሱ እስክንድር ተናግረዋል።

የጥምረቱ ስያሜ ‹‹ባልደራስ መኢአድ›› ተብሎ ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ኢህአዴግ መሸነፍ አለበት፣ ዴሞክራሲ መገንባት አለበት ብሎ የሚያን ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ጥምረቱን ለመቀላቀል በራችን ክፍት ነው ሲሉ እስክንድር ገልጸዋል።

መኢአድ አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ሲሆን ባልደራስ ደግሞ ክልል አቀፍ መሆን ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የግለሰቦች ስብስቦች እንዲሁም ግንባርና ቅንጅት መፍጠር የሚፈልጉ ፓርቲዎች አስፈላጊ ሰነዶቻቸውን እስከ የካቲት 30/2012 ድረስ እንዲያስገቡ መጠየቁ ይታወሳል።

 

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com