ከተለያዩ የዓለም አገራት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ መግባታቸውን ማወቅ ተችሏል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገጠር መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አመንቴ ገሺ ተናግረዋል በተባለው መሰረት፣ ከ60 የሚበልጡ ዳያስፖራዎች አሶሳ ከተማ መግባታቸው ነው የተገለጸው።
ከዳያስፖራዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ አስታውቀዋል የተባሉት ኃላፊው፣ የክልሉ ኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ገለጻ ይደረግላቸዋል ማለታቸውም ተመላክቷል።
ወደ አሶሳ ከተማ ገብተዋል የተባሉት የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላቱ በሦስት ቀናት ቆይታቸው የታላቁ ሕዳሴ ግድብን እንደሚጎበኙና የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጭ ሥፍራዎችን እንደሚመለከቱ ተናግረዋል ነው የተባለው።
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዐቢይ አሕመድን (ጠ/ሚ) ጥሪ ተቀብለው ወደ አገራቸው መግባታቸው የሚታወስ ነው።
ለዳያስፖራዎች የክልሉን የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚያስተዋውቅ ኤግዚቢሽን በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ መሆኑም ነው የተገለጸው።
ለሦት ቀናት እንደሚቆይ የተጠቆመው የፕሮሞሽንና ኤግዚቢሽን መርሃ ግብሩ፣ የክልሉን ዕምቅ ሀብት ለዳያስፖራው ማኅበረሰብ ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
ዳያስፖራዎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት በማንፋክቸሪኒግ፣ በአገልግሎት፣ በማዕድን፣ ኢንዱስትሪና በእርሻ ኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሠማሩም ጥሪ ቀርቦላቸዋል ነው የተባለው።
ቅጽ 4 ቁጥር 171 የካቲት 5 2014


