ታዋቂው የሆሊውድ ተዋናይ ቶም ሃንክስ እና ባለቤቱ በኮረና ቫይረስ ተያዙ

Views: 201

አሜሪካዊው ታዋቂ የሆሊውድ ተዋናይ ቶም ሃንክስ እና ባለቤቱ ተዋናይት ሪታ ዊልሰን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገለጸ።

ወደ አውስትራሊያ ሲያቀኑ ምርመራ ተደርጎላቸው የኮሮና ቫይረስ ምልክት እንደታየባቸው ቶም በኢንስታግራም ገጹ ላይ ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።

የ63 ዓመት አዛውንት የሆኑት ቶም እና ባለቤቱ በአሁን ወቅት የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ ተገልጿል።

ቶም ሃንክስ በፊልሙ ዘርፍ በተዋናይነት የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ካገኛቸው ሽልማቶች መካከል የኦስካር እና የአካዳሚ አዋርድ ተጠቃሽ ናቸው።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com