“በህወሃት ታጣቂዎች በአማራ ክልል የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት አሳስቦኛል“:- አሜሪካ

0
1459

ዕረቡ የካቲት 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በህወሃት ታጣቂዎች በአማራ ክልል በነሃሴ ወር መጨረሻ እና በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ የተፈጸሙ አሰቃቂ ድርጊቶች በእጅጉን እንዳሳሰባት አሜሪካ አስታወቀች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን ሪፖርት መሰረት አድርጎ ትናንት መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫውም ሁሉም የታጠቁ የግጭቱ ተዋናዮች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚያደርሱትን የሰብዓዊ መብት ረገጣ እና ጥቃት እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርቧል።

ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ይቻል ዘንድ፤ ለተፈጸመው ግፍ ተዓማኒነት ያለው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል የሚል የጸና አቋም እንዳለውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የጭካኔ ድርጊቶችን የሚገልጹ ሪፖርቶች አሁንም መውጣት መቀጠላቸው ግጭቱን በፍጥነት ማስቆም አስፈላጊ መሆኑን አጉልቶ ያሳያል ሲልም በመግለጫው አሳስቧል።

ስለሆነም የጭካኔ ድርጊቶች እንዲቆሙ፣ የህይወት አድን ሰብዓዊ እርዳታዎች ያለማቋረጥ እንዲሰጡ እና ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ለማሳሰብ በግጭት ውስጥ ያሉ አካላትን ማሳተፍ እንቀጥላለን ሲልም አስታውቋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here