አርብ የካቲት 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ትምህርት ሚኒስቴር የመረጃ፣ የተግባቦትና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሁም የዲጂታል ቴክኖሎጂ አተገባበር ሥርዓትን ማሻሻል የሚያስችሉ መርሐ ግብሮችን ይፋ አድርጓል።
የኦንላይን መማሪያ ሥርዓትን እና ዲጂታል ላይብራሪ አገልግሎቶቱ መደበኛና አጋዥ መጽሃፍት፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ትምህርት ሚኒስቴር ካዘጋጃቸው እና ለተማሪዎች ይጠቅማሉ ካላቸው ከተለያዩ የውጭ ምንጮች በማካተት ይዞ መቅረባቸውንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
አገልግሎቱ ለተማሪዎች ግብዓቶችን በክፍል፣ በትምህርት አይነት፣ በምዕራፍ በመምረጥ ለአጠቃቀም ቀላል ሆኖ መቅረቡም ነው የተገለፀው፡፡
በተጨማሪም የአካል ጉዳተኞችን እና ወደ ትምህርት ቤት መምጣት የማይችሉ ተማሪዎችን ችግር እንዲያቃልል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ልዪ ተሰጥኦ ያላችውን ተማሪዎች በትምህርት ሥርዓቱን ሳይገደቡ መከታተል ያስችላልም ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የመማር ማስተማር ግብዓቶችን በክፍል፣ በትምህርት አይነት እና በምዕራፍ ተከፋፍሎ ወደ ሥርዓቱ የመጫን ሥራ ተሰርቶ ግብዓቶቹን በነፃ በኢንተርኔት እና ከኢንተርኔት ውጪ በማውረድ መጠቀም ያስችላል፡፡
በቀጣይም ለመጀመሪያ ደረጃ እና የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች የዚሁ አግልግሎት ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ በፈጣን ሁኔታ እየተሰሩ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
ተማሪዎችም የኦንላይን መማሪያ ሥርዓትን እና ዲጂታል ላይብረሪ አገልግሎትን ለማግኘት የ https://elearn.moe.gov.et
አድራሻ መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




