በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ በቁጥጥር ሥር ዋለ

0
865

ሰኞ የካቲት 28 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ላይ ከትላንት ጀምሮ ተከስቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ።

በፓርኩ ላይ የደረሰውን የአደጋ ጉዳት መጠን ለመቀነስና እሳቱን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት የጋሞ ዞን፣ የአርባ መንጭ ከተማ እና አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊሶች፣ የጋሞ ዞን አካባቢ ደንና አኤር ንብረት ለውጥ ፅ/ቤት ሰራተኞች እንዲሁም በርካታ ሚኒሻዎች እና ሬንጀሮች በጋራ በተደረገ ርብርብ እሳቱን በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡

በፓርኩ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ መነሻው ከሰል ከሚያከስሉ እና እንጨት ለቀማ ከገቡ ሰዎች ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል የፖርኩ ሥራ አስኪያጅ ሽመልስ ዘነበ ገልጸዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here