ለመንገድ አገልግሎት የተቀመጠ ድማሚት ፈንድቶ የ7 ህጻናት ህይወት አለፈ

0
518

ሰኞ የካቲት 28 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ግራር ውኃ በተባለ ቀበሌ ለመንገድ አገልግሎት የሚውል ድማሚት ፈንድቶ የ7 ህጻናትን ህይወት ማለፉን የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ኃይሌ ብርሃኑ ገልጸዋል።

አደጋው የተከሰተው በየካቲት 27 ቀን 2014 ከምሽቱ 11:30 ገደማ ሲሆን፤ አደጋው የተከሰተው በሱር ኮንስትራክሽን ሲሰራ በነበር የመንገድ ፕሮጀክት የቁሳቁስ ካምፕ ላይ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል።

የቁሳቁስ ካምፑ ውስጥም የአካባቢው ህጻናት ለጭዋታ ሲገቡና ሲወጡ እንደነበርም ረዳት ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here