የበለስ ስኳር ፋብሪካ ስኳር ማምረት ጀመረ

0
815

ሐሙስ መጋቢት 1 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል በጃዊ ወረዳ የሚገኘው የበለስ ስኳር ፋብሪካ መደበኛ ስኳር በማምረት ሥራዉን ጀምሯል።

የፋብሪካዉን ምረት ማምረት ማሰጀመር ሥራ የፋብሪካዉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አንተነህ አሰጌ፣ ሁሉም የፋብሪካዉ ማኔጅመንት አካላትና የፈንደቃ ከተማ ከንቲባዎች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡

ፋብሪካዉ በዚህ ዓመት ከ1መቶ ሃምሳ ሺህ እሰከ 2 መቶ ሺህ ኩንታል ስኳር ያመረታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፋብሪካው ወደ ሙሉ ትግበራ ሲገባ በቀን 12 ሺህ ኩንታል ስኳር የማምረት፣ 45 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ በማምረት 17 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት ለፋብሪካው ማንቀሳቀሻ በመጠቀም፤ ቀሪውን የኤሌክትሪክ መጠን ለአገራዊ ቋት በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እንዲሁም ሞላሰስና ሌሎች ተረፈ ምርቶችን በመሸጥ ገቢውን ለማሳደግ ማቀዱም ተነግሯል፡፡

ለአካባቢው ማህበረሰብና ለአገሪቱ ዜጎችም አሁን ከፍተኛ የሆነውን የሥራ አጥነት ችግር በመፍታትም አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በቀጣይም ለ20 ሺህ ዜጎች ቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ይፈጥራልም ተብሏል፡፡
_________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here