“የብልፅግና ፓርቲ ችግሮችን በማለፍ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው”: – የፓርቲው ጽሕፈት ኃላፊ አደም ፋራህ

0
587

አርብ መጋቢት 2 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የብልፅግና ፓርቲ በለውጡ ሂደት በርካታ ፈተና ቢያጋጥሙትም ችግሮችን በማለፍ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር እየሰራ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ከፈተና ወደ ልዕልና በሚል መሪ ዓላማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባዔው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ በጉባዔው የፓርቲው አመራሮች የሚሰሩት ሥራ በጥራት እንዲያከናውኑ አቅጣጫ እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡

የተጀመረው አገራዊ ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተለያዩ ሥራዎች ፓርቲው እንደሚሰራም አመልክተዋል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ለዛሬና ለነገ ትውልድ የሚለፋ ፓርቲ ነው ያሉት የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አደም ፋራህ መፍትሔ ተኮር ፓርቲ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

የፓርቲው ጉባኤ በውስጥና በውጭ ጠላቶች የተደቀነውን ፈተናዎች በመቀልበስ የሚካሄድ መሆኑንም ማመልከታቸውን ዋልታ ዘግቧል፡፡

አደም ፋራህ ጉባኤው ፓርቲውን በአመራር፣ በአደረጃጀትና በአሰራር በማጠናከር የጀመረውን አገራዊ ለውጥ በማፅናት ረገድ የማይተካ ሚና እንደሚኖረውም አስረድተዋል፡፡
_________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here