“እንስራ” የተሰኘ ሥራ ማፈላለጊያ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ

0
852

ሐሙስ መጋቢት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) Trade Ethiopia Commissioning ከመርሲ ኮርፕስ ሊዌይ ጋር በመተባበር እንስራ “Enisra” የተሰኘ ሥራ ማፈላለጊያ የሞባይል መተግበሪያ በዛሬው ዕለት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ይፋ አደረገ፡፡

በአዲስ አበባ 20 ነጥብ 2 ከመቶ ሥራ አጥ ወጣቶች ሲኖሩ፤ ዕድሜያቸው ከ15-29 ያሉ ወጣት ሥራ አጦች ቁጥር ደግሞ 24.1 በመቶ እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

ሌሎች ጥናቶች እንደሚያሳዩት 50 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የቤት ውስጥ ሥራዎችን በመሥራት የሚያልፉ ሲሆን፣ በተመሳሳይ 59 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት በሥራ ፍለጋ ላይ ያሉ ናቸው ተብሏል፡፡

Enisra የተባለው የሞባይል መተግበሪያ በዋነኝት አነስተኛ ገቢ እና ክህሎት ላላቸው ሴቶች እና ወጣቶች ወጭ ቆጣቢ የሥራ ማፈላለጊያ ዘዴ ነው ሲሉ የTrade Ethiopia ዋና ሥራ አስፈጻሚ በርናባስ ወልደገብርዔል በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡

ከሞባይል መተግበሪያው በተጨማሪ ድረ ገፅ፣ የጥሪ ማዕከል እና በየወረዳው የሚቀመጡ ተንቀሳቃሽ ኪዮስኮች እንዳሉት በርናባስ ተናግረዋል፡፡

የሞባይል መተግበሪያውን መጠቀም ለማይችሉ ሥራ ፈላጊዎች በመዲናችን ባሉ 11 ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 10 ወረዳዎች የሥራ ኪዩስኮች ሥራ እንደሚያስጀምሩ የትሬድ ኢትዮጵያ ኦፐሬሽናል ማናጀር እና በእንስራ ፕሮጀክት ሲስተም ዴቨሎፐር እና የቡድን መሪ ሰማሃር ተስፋዬ መናገራቸውን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል፡፡
___________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here